ጉዞ ዓድዋ 6 የሐረር (ድሬ) ዘማቾች አዳማ ደርሰዋል

Google+ Pinterest LinkedIn Tumblr +

ጉዞ ዓድዋ 6 የሐረር (ድሬ) ዘማቾች አዳማ ደርሰዋል:: የአዲስ አበባው ጉዞ #ማክሰኞ ጥር 7 ይጀመራል። *እግራቸውን አጥበው አጅበው ለተቀበሉት የአዳማ ናዝሬት ወጣቶች ክብር ይሁን።

*የፊታችን እሁድ አዲስ አበባ የሐረር ዘማቾች (የድሬ ጀግኖችን) በታላቅ ክብር ትቀበላለች። *እሁድ ጥር 5 ቀን 2011ዓ.ም. ቸርችል ጎዳና መሐል ከቴውድሮስ አደባባይ ጀምሮ እስከ ጣይቱ ሄቴል ድረስ የአዲስ አበባ ወጣቶች አጅበው በመቀበል ጀግኖቹን ያነግሳል።

*ማክሰኞ ጥር 7 ቀን ማለዳ 1:30 በአዲስ አበባ ምክትል ከንቲባ ክቡር ኢንጂነር ታከለ ኡማ መሪነት ከአዲስ አበባ ወደ ዓድዋ የሚጓዙ ዘማቾችን ጨምሮ 42 ጀግኖች በርችል ጎዳና ትይዩ በር በማዘጋጃ ቤት ቅጥር ግቢ ውስጥ በታላቅ ክብር አሸኛኘት ይደረግላቸዋል። ሁሉም ሀገር ወዳድ ጀግኖቹን አጅቦ እንዲሸኝ ተጋብዟል።

*በፍቅር ተጀምሮ በፍቅር የሚጠናቀቀው የዘንድሮው ጉዞ ዓድዋ 6 ለመጀመር በአንድ መዳፍ ጣቶች የሚቆጠሩ ቀናት ብቻ ቀርተዋል። ቸር አምላክ ኢትዮጵያ ይባርክ! *ፀሐይ ተጠብሶ ተጓዦችን ውሀ ለማጠጣት የአዳማን በር በር እያየ ሲጠባበቅ የዋለውን ገጣሚ አደም ሁሴንን በእጅጉ እናመሰግናለን።

ምስጋና፦ ሀብታሙ መንገሻ የአዳማ ገልማ አባ ገዳ ም/ ዳይሬክተር አቶ ጀማል የአዳማ ከተማ ልዩ ሀይል ሀላፊ
ከልባችን እናመሰግናለን።

“ፍቅር ለኢትዮጵያ”
“ኢትዮጵያዊነት_ይለምልም!!”

አዘጋጆቹ

Share.

About Author

Leave A Reply