ጋዜጠኛ ሲሳይ አጌና የተናገረው ስህተት ብቻ አይደለም። ወንጀልም ነው

Google+ Pinterest LinkedIn Tumblr +

ቤታቸው ሊበረበር እንደሚችል ሲያውቁ መንግስትን ለማሳጣት ብለው እንደዚ አይነት ነገር ሁሉ ሊያዘጋጁ ይችላል ተብሎ ነው መታመን ያለበት። ደብተሩን እንደዚህ አይነት የፌክ ነገር ሁሉ አድርገው ሊያስቀምጡ ሁሉ ይችላሉ ብሎ ማሰብ ያስፈልጋል። ሲሳይ አጌና

የምናከብራቸው ሰዎች ሁሉ ገዥዎችን እንከላከላለን እያሉ ትዝብት ውስጥ እየገቡ ነው። ጋዜጠኛ ሲሳይ አጌና እነ ዐቢይ የሚያጠፉትን ለመከላከል ሲጥር ትዝብ ውስጥ እየገባ ነው። ጋዜጠኛ ሲሳይ አጌና እንዲህ ግልፅ የሆነውን ቀርቶ በርካታ የሴራ ትንታኔዎችን ሲያስረዳ የኖረ ሰው ነው። ቤተ መንግስት ደርሶ ከሄደ በኋላ ግን ትልቅ ትዝብ ውስጥ ገብቷል። ለአብነት ትናንት የተናገረውን ብናይ በክፉው ዘመን የተከበሩ ሰዎች ደሕና በተባለለት ቀን ደሕና ባይሆንም እንዲህ ራሳቸውን ማስገመታቸው ሚስጥር ምን ይሆን ያስብላል።

ሲሳይ ብርጋዴር ጄነራል አሳምነው ፅጌን ባለቤት ያላግባብ ወንጅሏል። መንግስት አማራውን ለመወንጀል በጥድፊያ የሰራውን ስህተት ለማስተባበል ራሱን ዝቅ የሚያደርግ የካድሬነት ተግባር ነው የፈፀመው። የብርጋዴር ጄነራል አሳምነው ባለቤት ሆን ብላ የባንክ ደብተሩ ላይ የተሳሳተ መረጃ ስለፃፈች ነው ይለናል ጋዜጠኛ ሲሳይ። መርማሪ የሚባሉት ይህን የተበላሸ የባንክ ደብተር እያዩ ዶክመንተሪ መግለጫ ላይ እንዴት ያካትቱታል ቢባል ሲሳይ መልስ የለውም። ዶክመንተሪውንም የብርጋዴር ጄነራል አሳምነው ሚስት ሰራችው ሊለን ነው

የሲሳይ ትልቁ ስህተት መንግስትን ለመከላከል ይህን ያህል ርቀት መሄዱ አይደለም። በእስር ላይ ያሉትን የብርጋዴር ጄነራል አሳምነው ፅጌ ባለቤት መንግስት ባልጠረጠራቸው ጉዳይ መወንጀሉ ነው። መንግስትን አሳስተዋል ተብሎ መታመን አለበት እያለ ነው። ባልተጠራበትና ባልተከሰሱበት ምስክር መሆኑ ነው። ይህ ደግሞ ወንጀል ነው። በሕግ ጥላ ስር ባለ ሰው ከፍርድ ቤት ቀድሞ እየፈረደ ነው። ጋዜጠኛ ሲሳይ አጌና በማያውቀው ነገር በታሰረ ሰው ላይ ይህን ግምት ከሰጠ ገዥዎች ገንዘብ ሰጥተው በሀሰት በሚያስመሰክሯቸው ካድሬና ደሕንነቶች የሚያደርጉት ላይገርመን ነው።

በእርግጥ የሲሳይ የወንጀል ምስክርነት ገዥዎቹ ከሚቀጥሯቸው የሀሰት ምስክሮችም የባሰ ነው። እንደ ሲሳይ ምስክርነት ከሆነ ብርጋዴር ጄነራል አሳምነው ባለቤት የባንክ ደብተሩንም በፎርጅድ ሰርተውት ሊለን ነው።

ሲሳይ የሚደግፈው መንግስት ደግሞ ምንም ይፃፍበት ምን እየወሰደ ዶክመንተሪ ይሰራበታል ማለት ነው። ሲሳይ አጌና እንዲህ ደንባራ የሆነ መንግስት ነው የሚደግፈው ማለት ነው።

ጌታቸው ሽፈራው

Share.

About Author

Leave A Reply