ግልጽ ደብዳቤ ለአቶ ለማ መገርሳ፣ የኦሮሚያ ክልል ፕሬዚዳንት

Google+ Pinterest LinkedIn Tumblr +

(የግል አስተያየት)

በህዝባችን ተወዳጅ የሆኑት የወያኔን የሰቆቃ አገዛዝ ለማስወገድ “ጣና የኛ” ያሉትን የኦሮሞ ወጣቶች (ቄሮ )ይዘው የህዝቦችን አንድነት ተግባራዊ ያደረጉት ዶ/ር ለማ መገርሳ የተሳሳቱበትን ከመሽሽግ ይቅርታ መጠየቁ በፈጣሪም በህዝብም ብድራት አለው::

በሃገራችን ኢትዮጲያ ታሪክ በቀደሙት ዘመናት በብዙ ሃገራዊ ጉዳዮች የመሬት ይዞታ እንዲስተካከል ለንጉሱ ፓርላማ አቤቱታ ያቀረበች በሃገሪቱ በድርቅ የተጎዱ ወገኖችን ከሌሎች ሃይማኖት መሪዎች ጋር በመቀናጀት በክፉ ቀን የደረሰች ወያኔ ስልጣን በያዘበት ሰሞን ለሃገራዊ እርቅና ሰላም ከሌሎች ጋር በግዮን ጉባኤ የተገኘት ወንጌላዊት መካነኢየሱስ ቤተክርስቲያን የወያኔ ክፉ የጎሳ ፖለቲካ ሳይተገበር በፊት በቅን መንገድ ለብዙሃኑ ወገናችን መብትና ማንነት የሰላም የፍትህ ትግል ተዋጽኦ ተሳታፊ ፋና ወጊም እንደነበረች የሃገሪቱን የመጀመሪያ ታሪክ ከጻፉት የዚህችው ቤተክርስቲያን ምሁር አለቃ ታዬ ጀምሮ የተመሰከረ ነው:።

ወደሃገራችን ገብተው ወንጌሉን ለመስበክ ወደኦሮሞ ዘንድ ሂዱ የተባሉትና ከወንጌል በተጨማሪ የመጀመሪያውን ዘመናዊ ትምህርት ቤት የጀመሩ በጤና ጭምር በህዳር በሽታ ብዙ ወገኖቻችንን በማከም ያተረፉና በዚያው በሽታ ህይወታቸው በሃገራችን ያለፈ ስዊዲናዊ ቄስ ሰደርስኩዊትና ሌሎቹንም ብዙ ያፈራች ቤተክስርቲያን የተፈጠረባት ተመሳሳይ ችግር ለሀጋራችን የነበራት በጎ መክሊት መወሰዱን ጸሃፊያን አማረ ማሞና መሰሎቹ መስክረዋል::

ኖም ግን ከንጉሱ አገዛዝ መውደቅ ዋዜማ ጀምሮ ውስጥውስጡን የሚካሄደው ትግል በጎ መስመሩን ስቶ በቤተክርቲያኒቱ ብዙሃን ነን የሚሉ በምክክርና ውይይት ሊፈታ የሚችለውን የቋንቋ አጠቃቀም መብት በማዛባት ችግርና ጉዳት እንደደረሰባት ይታወቃል።

የመካነኢየሱስ መሪዎች የፈጸሙት ስህተት ለዶ/ር ለማ መገርሳና ለባልደረቦቻቸው ምሳሌ ሆኖ በጀመሩት በጎ ቅን ራእይ በተገቢው መንገድ የኦሮሞ ወገናችንንም ሆነ የጠቅላላዋ ኢትዮጲያን ጉዳዮች በሚዛናዊነት ያለወገናዊነት በመፈጸም በታሪክ የተመዘገበ በጎ ስራቸውን ይጠብቁ ዘንድ ያላስፈላጊ የዘር ጥላቻና እልቂት በተለያዩ አቅጣጫዎች ከሚዘሩ ጽንፈኞች ፉክክርና ትብብር ያቆሙ ዘንድ ወቅታዊ ምክሬን ሰጣለሁ:: ዲጎኔ ሞረቴው ከኩሽቲክ ሴማቲክ ኦሞቲክ ድብልቅ ኢትዮጲያያዊያን ተሃድሶ ህብረት ሀጢያቱን የሚሰውር አይለማም የሚናዘዝባትና የሚተዋት ግን ምህረትን ያገኛል ምሳሌ 28:13

(ዳኜ ወረታው)

Share.

About Author

Leave A Reply