ግልፅ መልዕክት ወዳጅም ጠላትም እንዲያውቀው (ገነት ጎይቶም በርሄ)

Google+ Pinterest LinkedIn Tumblr +

ይህን ነገር ልግለፀው አልግለፀው ብዬ ከራሴ ጋር ብዙ ተሟግቻለሁ። አሁን ግን ከዝምታ መናገር ይሻላል የሚያስብለኝ ሁኔታ ስለተፈጠረ ነው።

ወላጅ አባቴን በስምና በፎቶ ካልሆነ አላውቀውም ገና በሶስት ወሬ ነው ‘ትግራይ ተበድላለች’ ብሎ ወደ በረሃ የሄደው። እናታችን ከእኔ ጋር አራት ልጆች ይዛ ኑሮን ተጋፈጠች።

እሱም እዚያ ብዙም አልቆየም ይባላል በ73 ዓም ሞተ። በልጅነት ዕድሜ ያለ አባት ማደግ አባቴ መቼ ይመጣ ይሆን ብሎ በናፍቆት መወዝወዝ ምናልባት የደረሰበት ያውቀው ይሆናል።

ህወሓቶች እዚህ መጥተው የስልጣን ወንበር እስኪቆናጠጡ መሞቱንም አናውቅም።_ በኋላ ግን መሞቱን ሰማን ህይወትም ቀጠለች በዚህ መሀል የት ናችሁ እንዴትስ ሆናችሁ ያለንም አልነበረም እንደለመድነው በእናታችን አጋዥነት ትምህርታችንን ቀጠልን እዚህ ያለንበት ለመድረስ ተግዳሮቱ ቀላል አልነበረም በስንት መውደቅ መነሳት እዚህ ደርሻለሁ።

ታዲያ እዚህ ፌስ ቡክ ላይ ራሴን ገልጬ መፃፍና መሳተፍ ከጀመርኩበት ጊዜ አንስቶ በትግራይ ልጆች ስሰደብ ና ስዋረድ ያለ ስሜ ስም ሲሰጠኝ ነው የቆየሁት።

ስለትግራይእና ትግራዋይ እናስባለን ጠበቃ ነን ይላሉ ግን ከሃሳባቸው ጋር የማይሄደውን ትግራዋይ ይሳደባሉ ያዋርዳሉ። እኔ ስቃወም በምክንያት ነው በማውቀውና በደረሰብኝ ነገር ነው። አባቴ ከህወሓት ጋር ሆኖ ሞቷል ነገር ግን የሱ ሞት አይደለም የኢትዮጵያንና የትግራይን ችግር የኛን የልጆቹንም ችግር አልፈታም።

ህወሓት ቤት(በአጠቃላይ የትግራይ ፖለቲከኞች ዘንድ ያለው አስመሳይነት ስለሚያናድደኝ ነው የምሞግታችሁ እንጂ ቁራጭ ሳንቲም የሚሰጠኝ የለም።

ይህን ስፅፍ በህወሓት ተከድቻለሁ በሚል ስሜት ሳይሆን አባቴ ቀድሞም የተሳሳተና የማይሆን የህይወት መስመር መከተሉን እያሰብኩ በማዘን ነው (የህወሓት አጭበርባሪነት እንዳለ ሆኖ ማለት ነው)

የህወሓቶች ነገር እንዲህ መጨመላለቁን እያየሁ አባቴ የሞተው እንዲህ ያለውን ስርዓት ለመፍጠር በመሆኑአር ፎ እኛን ልጆቹን ማሳደግ ነበረበት የሚል ቁጭት ሁሌም ውስጤ አለ።

እዚህ ካሉት አስመሳይና ሆድ_አደር ስርዓት አልበኛ የህወሓት ጀሌዎች ጋር የሚያጨቃጭቀኝም በማያውቁት ነገር ገብተው መፈትፈት ሲፈልጉ ነው። ።

ጨካኝም በሉኝ ውሸታም እንደፈለጋችሁ፦

በአንድ ነገር ግን እፅናናለሁ አባቴ ተመልሶ አሁን እንደምናያቸው ዓይነት አገር አጥፊ የህወሓት ሰዎች ሆኖ ከሚያሳቅቀኝ በዚያው መቅረቱ የተሻለ ነው እላለሁ።

መጀመሪያውኑም ህወሓት የተባለች የማፊያ ቡድን ባይቀላቀል ደግሞ የበለጠ መልካም ነበር። የትግራይ ልጆች የሆናችሁ የፌስቡክ አርበኞች የእናንተ ዓይነቱን ትዕቢተኛና ትምክህተኛ ትውልድ አባቴ በሞተበት ቡድን አስተምህሮ ተፈጥሮ በማየቴ ይበልጥ አዝናለሁ።

Share.

About Author

Leave A Reply