ጠቅላይ ሚኒስተር ዶ/ር አብይ አህመድን ለመግደል አሰበዋል ከተባሉ ግለሰቦች አንዱ ጌቱ ግርማ ማንነት

Google+ Pinterest LinkedIn Tumblr +

ሰኔ 16 2010 ዓ.ም ጠቅላይ ሚኒስተር ዶ/ር አብይ አህመድን ለመግደል አሰበዋል ከተባሉ ግለሰቦች ውስጥ የቦንብ ጥቃት አድርሰዋል ተብለው ትናንት ከተከሰሱት ግለሰቦች አንዱ ነው ጌቱ ግርማ ነው ። አቶ ጌቱ ግርማ በ2008 ዓ.ም በእነ ጉርሜሳ አያና (እነ በቀለ ገርባ ያሉበት ማለት ነው) ክስ መዝገብ በፀረ ሽብረተኝነት ወንጀል ተከሶ የጥፋተኝነት ውሳኔ ተላልፎቦት እንዲከላከል የፌደራል ከፍተኛው ፍ/ቤት 4ኛ ወንጀል ችሎት ወስኖ የነበረ ቢሆንም መንግስት ለህዝብ ጥቅም ሲባል ክሱ በጠቅላይ ዐ/ህግ ተነስቶ ከ ሰባት ወር በፊት መፈታቱ ይታወቃል። አሁን ደግሞ በሰኔ 16 የድጋፍ ሰልፍ ላይ ጠቅላይ ሚኒስተሩን አብይ አህመድን ለመግደል ኬንያ አገር ከምትገኘው ገነት ታምሩ ( በቅፅል ስሟ ቶለሽ ታምሩ) ተልኮ ተስጥቶት ድርጊቱን ፈፅሟል ብሎ ጠቅላይ ዐ/ህግ ክስ መስርቶበታል።

(መንበረ ካሳዬ)

Share.

About Author

Leave A Reply