ጠቅላይ ሚኒስትሩ: በምልአተ ጉባኤው ላይ ተገኝተው ቅዱስ ሲኖዶስ ቤተ ክህነቱን እንዲያጠናክር ጠየቁ

Google+ Pinterest LinkedIn Tumblr +

የቅዱስ ሲኖዶስ ምልአተ ጉባኤ የርክበ ካህናት ስብሰባውን በጀመረበት፣ ዛሬ ረቡዕ፣ ግንቦት 14 ቀን 2011 ዓ.ም.፣ ከቀትር በኋላ፣ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ተገኝተው ንግግር አድርገዋል፡፡ የዶ/ር ዐቢይ አሕመድ ንግግር በሚከተሉት ነጥቦች ላይ ማተኮሩ ተጠቁሟል

መንግሥቴ፣ ቤተ ክርስቲያኒቱን ያከብራል፤ ባለ በሌለ አቅሙ ይደግፋታል፣ የአንድነት ጉባኤ የኾነው ቅዱስ ሲኖዶስ በዘረኝነት ከወደቀ “ክርስቶስን ረሳ፣ በአስተዳደራዊ ችግር እና በሙስና በየፍ/ቤቱ የሚንገላቱ ካህናትን ታደጉ፣ ሕዝቡን አስተዋውቁ፤ አዋሕዱ፤ የሰላም መሪዎች እንድትኾኑ እንሻለን፣ ቤተ ክርስቲያን ዛፎችን መትከል ብቻ ሳይኾን መጠበቅም ታውቅበታለች፣ በመጪው ወርኀ ክረምት 4 ቢልዮን ችግኞችን እንተክላለንና አግዙን፣ ክርስቲያኑ ምእመን የሙስሊሙን፣ ሙስሊሙ የክርስቲያኑን ደጅ ያጽዳ፣ በረመዳን ፍቺና በመስቀል በዓል ይህን እናድርግ፤ ፍቅርን እናስተምር።

ምልአተ ጉባኤው፣ በቀትር በፊት የመጀመሪያ ቀን ውሎው፣ የቅዱስነታቸውን የመክፈቻ ቃለ ምዕዳን ከአደመጠ በኋላ፣ ሰባት አባላት ያሉት አጀንዳ አርቃቂ ኮሚቴ ሠይሟል፤ ከቀትር በኋላ ውሎው፣ ኮሚቴው የሚያቀርባቸውን የመነጋገሪያ ነጥቦች በማጽደቅ መወያየቱን ይቀጥላል፡፡

በአርቃቂ ኮሚቴው ብፁዕ አቡነ እስጢፋኖስ፣ ብፁዕ ዶር. አቡነ ኤዎስጣቴዎስ፣ ብፁዕ አቡነ ሩፋኤል፣ ብፁዕ አቡነ መቃርዮስ፣ ብፁዕ አቡነ ቴዎፍሎስ፣ ብፁዕ አቡነ ጴጥሮስ(ምዕ. አውስትራልያ) እና የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊ ብፁዕ አቡነ ሳዊሮስ በአስረጅነት እንደሚገኙበት ታውቋል፡፡

(ምንጭ ሐራ ተዋህዶ)

Share.

About Author

Leave A Reply