ጠቅላይ ሚኒስትሩ ነገ ወደ ባሌ ያመራሉ

Google+ Pinterest LinkedIn Tumblr +

የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ በነገው እለት ወደ ኦሮሚያ ክልል ባሌ ዞን ያቀናሉ።

ከጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር እብይ ጋርም የኦሮሚያ ክልል ርእሰ መስተዳደር አቶ ለማ መገርሳ ወደ ስፍራው እንደሚያቀኑ ተነግሯል።

በነገው እለት ጠዋት ላይም በሮቤ ስታዲየም ከዞኑ የተለያዩ አካባቢዎች ለተውጣጡ ነዋሪዎች ንግግር እንደሚያደርጉም ይጠበቃል።

በመቀጠልም ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ እና የኦሮሚያ ክልል ርእሰ መስተዳደር አቶ ለማ መገርሳ ከባሌ ዞን ከተወጣጡ ቁጥራቸው 850 ከሚደርሱ የህብረተሰብ ተወካዮች ጋር የሚወያዩ ይሆናል።

በዚህ የውይይት መድረክ ላይም በዞኑ የኢኮኖሚያዊ፣ ፖለቲካዊ እና ማህበራዊ ችግሮች እንዲሁም በቀጣይ አቅጣጫዎች ላይ ትኩረት ያደረገ ምክክር እንደሚያካሂዱም ነው የሚጠበቀው።

ምንጭ፤ ፋና

 

Share.

About Author

Leave A Reply