ጠቅላይ ሚኒስትሩ ዛሬ ለፓርላማው ያቀረቧቸው ዋና ዋና ነጥቦች

Google+ Pinterest LinkedIn Tumblr +

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ በዛሬው እለት በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ተገኝተው ማብራሪያ በመስጠት ላይ ናቸው።

የምክር ቤት አባላቱ በተለያዩ ወቅታዊ ጉዳዮች ላይ ያተኮሩ ጥያቄዎችን ለጠቅላይ ሚኒስትሩ አቅርበዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩም ማብራሪያ በመስጠት ላይ ይገኛሉ።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በንግግሯቸው ካነሷቸው ነጥቦች መካከል፦

• 20 የሚጠጉ የታጠቁም ያልታጠቁ የፖለቲካ ፓርቲዎች ወደ ሀገራቸው ተመልሰዋል።

• የቀረበው የሰላም ጥሪ የሰላም መርህን የተከተለ ነው፤ ከእነዚህ ፓርቲዎች ጋር የተደረጉ ድርድሮችም በዚህ መሰረት የተከናወኑ ናቸው።

• የገቡት ፓርቲዎች የተሻለ ሀሳብ አምጥቶ ሀገሪቱን ከድህነት የሚያወጣ፤ ሰላሟን የሚያረጋግጥ ሀሳብ ማፍለቅ አለባቸው።

• የኢትዮጵያ ሉዓላዊ ግዛት ለድርድር አይቀርብም። መንግስት በኢትዮጵያ ሉአላዊነት ዙሪያ ከማንም ጋር አይደራደርም። ህግን ተመስርተን እርምጃ እንወስዳለ።

• ወደ ሀገር ውስጥ ከገቡት የተፎካሪ ፓርቲዎች አብዛኛዎቹ ዴሞክራሲ በሀገሪቱ እንዲሰፍን እየሰሩ ነው ሆኖም ከገቡት መካከል ጉራማይሌ የሆነ ባህሪ ያላቸው አሉ፤ ይህ ጉራማይሌ አካሄድ መቆም ይገባዋል፡፡

• ችግር እየፈጠሩ ተጠቃሚ ለመሆን የሚጥሩ አካላት አሉ።

• በአሁኑ ወቅት የፓለቲካ ምህዳሩ ሰፍቷል በዚህም የረጅም ርቀት ለመሮጥ ትንፋሽ የሚያጥራቸው ፓርቲዎች አሉ።

• አሁን የሚያስፈልገው ኢትዮጵያ አንድነቷን፣ ሰላሟን እና ሉዓላዊነቷን ለማረጋገጥ የሚያስችል ሀሳብ ያለው ፓርቲ ነው።

• በኢትዮጵያ አንድነት የሚገዳደር ሀይል ካለ በኢትዮጵያ ጦርነት አውጇል ማለት ነው። በዚህ ጉዳይ መንግስት እርምጃ ይወስዳል፡፡

• የሀገር አንድነት፣ ዴሞክራሲን እና ሰላምን የማስፈን ሀላፊነት የሁሉም ዜጋ ነው።

• መንግስትን መተቸት ይቻላል ነገር ግን የኢትዮጵያ እንድነት እና ሉአላዊነትን መተቸት አይቻልም።

• የመከላከያ ሰራዊት ዋና ስራው የሀገሪቱን ሉዓላዊነት ማስከበር ነው። ሆኖም በክልሎች ከአቅም በላይ የሆነ የፀጥታ ችግር ሲፈጠር እና ጥያቄ ሲቀርብለት ሰላምን ያሰፍናል። ምርጥና የተሻለ ስራ ከሰሩት ተቋማት መካከል ቀዳሚው መከላከያ ነው።

• በየአካባቢው የሚገኙ ቀበሌዎች፣ ወረዳዎች የሚነሱ ግጭቶችን በመከላከል ሰላምን የማረጋገጥ ሀላፊነት የክልል መንግስታት ነው፡፡

• ለዚህም መንግስት በዚህ አመት ከፍተኛ የበጀት ድጎማ አድርጓል፡፡

• እውነት እና ሀሳብ ነው በአሁኑ ወቅት ለኢትዮጵያ የሚያስፈልገው፡፡

• ህዝቡ ህገወጥ ናቸው የሚለውን የታችኛውን እርከን ህገወጥ በሆነ መንገድ ለማንሳት መንቀሳቀስ የለበትም።

• የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ተማሪዎች የፖለቲካ ሀይሎች መጠቀሚያ እንዳይሆኑ ማድረግ በመጀመሪያ የተማሪዎች ሀላፊነት ነው። ከተማሪዎች የሚጠበቀው ሀሳብና ሀሳብን አጋጭቶ የተሻለ ሀሳብ ማውጣት እንጅ ድንጋይና ድንጋይን አጋጭቶ እሳት ማውጣት አይደለም።

Share.

About Author

Leave A Reply