ጠቅላይ ሚኒስትሩ ደቡብ ሱዳንን አስጠነቀቁ

Google+ Pinterest LinkedIn Tumblr +

ትናንት ማምሻውን የምስራቅ አፍሪካ በይነ መንግስታት (ኢጋድ) ለአስቸኳይ ስብሰባ በአዲስ አበባ ተቀምጧል።

የቡድኑ ዋነኛ አጀንዳ የደቡብ ሱዳን ጉዳይ መሆኑ ነው የተነገረው።

በዚሁ ስብሰባ ላይ ነው የኢትዮጵያው ጠቅላይ ሚኒስትር አቢይ አህመድ የደቡብ ሱዳንን መንግስትና ተቃዋሚዎችን ያስጠነቀቁት።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በንግግራቸው “ከዚህ ቀደም በርካታ ስምምነቶች በርካታ ቃሎች ተገብተው ተሽረዋል። አሁን ግን በዚሁ እንዲቀጥሉ አንፈቅድም። የደቡብ ሱዳን መንግስትም ሆነ ተቃዋሚዎች የህዝባቸው ጉዳት የማይሰማቸው ከሆነ አንድ ነገር በደንብ ግልጽ ሊሆንላቸው ይገባል። አንታገሳቸውም። ማንኛውንም እርምጃ ለመውሰድ የሞራልም ሆነ የህግ ድጋፍ እንዳለን ማወቅ አለባቸው።” በማለት ተናግረዋል።

በስብሰባው ላይ ፕሬዚዳንቱ ሳልቫ ኪርና ተቃዋሚያቸው ሬክ ማቻር ተገኝተዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከዚህ ስብሰባ አስቀድሞ ረቡዕ እለት ከሁለቱም ጋር ውይይት ያደረጉ ሲሆን በዚህ ውይይታቸው እንዳልተደሰቱ ነው የተዘገበው።

Share.

About Author

Leave A Reply