ጠቅላይ ሚኒስትር አብይን ለመደገፍ በቂ ምክንያት አለኝ ! ቴዎድሮስ ተ/አረጋይ

Google+ Pinterest LinkedIn Tumblr +

በዶ/ር አብይ የስልጣን ጊዜ ይሄኔ ኮ/ል መንግሥቱ እና አቶ መለስ ተቃዋሚዎቻቸውን በመግደልና ማሰር ላይ ተጠምደው ውለው ያድራሉ ። እኚህኛው ግን የእነሱ የሀጢአት እድፍ አጽድተው ዘና ብለው ሀይል ለማሰባሰብ በየሀገሩ ይዞራሉ ። ” ባዶ ካዝና ነው የተረከብናው ” እያሉ ከማለቃቀስ ይልቅ ወጣ እያሉ ፣ ከስልጣናቸው ዝቅ እያሉ ፣ እየለመኑም ቢሆን በሙስና የተራቆተውን ካዝና በብር ለመሙላት ይታትራሉ ። የቀደሙት የበተኑትን ዜጋ እየዞሩ ይሰበስባሉ ።

ከጥላቻና ድንፋታ ይልቅ ጠላቶቻቸውን በመውደድ ላይ ተጠምደው ይታያሉ ። መግለጫ ቢወጣባቸው ሲያንሳቸው ነው ። ገና ሌላ ዱለታም ይጠብቃቸዋል ። በሐገር ውስጥም ይሁን በውጭ የጠቅላይ ሚኒስትሩን አስተዳደር በግልጽ የነቀፈ ተቃዋሚ ያየሁት ሕወሓትን ብቻ ነው ። እኚህ ሰው ልሰር ብለው ቢነሱ በቂ ምክንያት አላቸው ። ሕዝብም ይደግፋቸዋል ። ግን ” ፍቅር ያሸንፋል ! ” ነው ያሉት እንደ ድምጻዊ ቴዎድሮስ ካሳሁን ። እናም እያሸነፉም ነው ።

ጅቦቹ ቢጮሁም ግመሉ ግን መንገዱን ቀጥሏል ። አሁን ሰውየውን የምደግፍበት በቂ ምክንያቶች አለኝ ። እናም ዶ/ር አብይ አሕመድን እንደ ሀገሬ ጠቅላይ ሚኒስትር አድርጌ አቀበላቸዋለሁ ። የኔ መሪ ናቸው ። ወድጄና ፈቅጄ እመራላቸዋለሁ ። የተሳሳቱ ሲመስለኝ ደግሞ በግልጽ እቃወማቸዋለሁ ። ስቃወምም ግን እደግፋቸዋለሁ ።

 

Share.

About Author

Leave A Reply