ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ ለስራ ጉብኝት ትናንት ማምሻውን ካይሮ ገብተዋል።

Google+ Pinterest LinkedIn Tumblr +

ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ የግብጹ ፕሬዚዳንት አብዱል ፈታህ አል ሲሲ በብሄራዊ ቤተ መንግስት ደማቅ አቀባበል አድርገውላቸዋል።

በግብጽ ቆይታቸው ከፕሬዚዳንት አብዱል ፈታህ አል ሲሲ ጋር በሁለትዮሽ፣ በአካባቢያዊና ዓለም አቀፋዊ ጉዳዮች ላይ ይመክራሉ ።

ኢትዮጵያና ግብጽ የቆየ የታሪክና የባህል ትስስር ያላቸው ሲሆን፤ የኢኮኖሚያዊና ፖለቲካዊ ግንኙነታቸውን በከፍተኛ ደረጃ ለማሳደግ በተለያዩ ጊዜያት እየተገናኙ ይመክራሉ።

ከሁለት ወራት በፊት በጠቅላይ ሚኒስትርነት የተሰየሙት ዶክተር አብይ አህመድ ወደ ስልጣን ከመጡ ጀምሮ ኡጋንዳን ጨምሮ በጅቡቲ፣ በሱዳን፣ በኬንያ፣ ሳዑዲ ዓረቢያ ፣ የተባበሩት ዓረብ ኤምሬቶች የስራ ጉብኝት አድርገዋል።

በጉብኝታቸው ወቅትም ከየአገሮቹ ጋር በሁለትዮሽ ግንኙነትና አካባቢያዊና ዓለምአቀፋዊ ጉዳዮች ላይ ተወያይተዋል፤ የየአገሮቹን ትስስር የሚያጠናክሩ ስምምነቶችንም ፈጽመዋል።

 

Share.

About Author

Leave A Reply