ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ ከቡራዩ የተፈናቀሉ ዜጎችን ጎበኙ

Google+ Pinterest LinkedIn Tumblr +

የኢፌደሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ ከቡራዩ ከተማ ተፈናቅለው በመድሃኒዓለም ትምህርት ቤት የሚገኙ ዜጎችን ጎበኙ።

በጉብኝቱ ወቅትም ተፈናቃዮቹ ለጠቅላይ ሚኒስትሩ ስሜታቸወን ያጋሩ ሲሆን፥ የተፈፀመባቸውንም ድርጊት አስረድትዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በጉብኝታቸው በደረሰው ነገር እጅግ ማዘናቸውን ገልፀዋል።

እንዲህ ዓይነት ድርጊት ቀጣይነት የለውም ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፥ በዚህ ድርጊት ፈፃሚዎች ተጠያቂ እንዲሆኑ መንግስት ጠንካራ እርምጃ ይወስዳል ብለዋል።

ተፈናቃዮቹ ወደ ቀያቸው በፍጥነት ተመልሰው እንዲቋቋሙ እንደሚደረግም ቃል ገብተዋል።

በፀጋዬ ንጉስ

Share.

About Author

Leave A Reply