ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ በነገው ሰልፍ ላይ ይገኛሉ

Google+ Pinterest LinkedIn Tumblr +

የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ ወደ ኃላፊነት ከመጡ በኋላ ላመጧቸው ለውጦች ድጋፍ እና እውቅና መስጠትን ዓላማ ባደረገው በነገው የአዲስ አበባ ሰልፍ ላይ ይገኛሉ።

የመንግስት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ፅህፈት ቤት ኃላፊ ሚኒስትር አቶ አህመድ ሽዴ ዛሬ በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ መግለጫ ሲሰጡ እንደተናገሩት፥ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ በሰልፉ ላይ እንዲገኙ የተጋበዙ ሲሆን እሳቸውም ተገኝተው ንግግር ያደርጋሉ።

የሰልፉ ዋና ዓላማ በሀገሪቱ አሁን ላይ የመጣውን ለውጥ በማበረታታት እውቅና መስጠት ነው።

በአጠቃላይ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ኢትዮጵያውያን ከጎናቸው መሆናቸውን ለማረጋገጥ ያለ ልዩነት የሚሳተፉበት እንደሚሆንም ይጠበቃል።

በዚህ ሰልፍ ኢትዮጵያ ቀጣይ ሰላሟ እንዲረጋገጥ መላው ኢትዮጵያውያን በዚህ ሰልፍ ላይ በመሳተፍ አጋርነታቸውን እንዲያሳዩም ነው ኮሚቴው የጠየቀው።

ሰልፉ ነገ ቅዳሜ ከጠዋቱ 1 ሰዓት ጀምሮ በመስቀል አደባባይ እንደሚካሄድ እና ከመዲናዋ በተጨማሪ በአዲስ አበባ ዙሪያ የሚገኙ ነዋሪዎች ይሳተፋሉ ተብሎ እንደሚጠበቅ ተገልጿል።

በባሃሩ ይድነቃቸው

 

Share.

About Author

Leave A Reply