ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ ዛሬ ወደ ሳዑዲ አረቢያ ያቀናሉ

Google+ Pinterest LinkedIn Tumblr +

የኢፌዲሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ በሳዑዲ አረቢያ ይፋዊ የስራ ጉብኝት ለማድረግ ዛሬ ወደ አገሪቱ ያቀናሉ።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ በሳዑዲ ጉብኝት የሚደርጉት የሀገሪቱ ንጉስ ቢን ሳልማን አብዱልአዚዝ ባደረጉላቸው ግብዣ መሰረት መሆኑን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ጽህፈት ቤት አስታውቋል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ በመካከለኛው ምስራቅ በሚያደረጉት የመጀመሪያ ጉብኝታቸው ከሀገሪቱ ባለስልጠናት ጋር በሁለትዮሽና አካባቢያዊ ጉዳዮች ዙሪያ ውይይት እንደሚያደርጉም ይጠበቃል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ በተመረጡበት ወቅት የደስታ መግለጫ ከላኩ አገሮች ውስጥ ሳውዲ አረቢያ በመጀመሪያ ረድፍ ትገኛለች።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ቀደምሲል በጅቡቲ፣ ሱዳን እና ኬንያ እና ጉብኝት ማድረገቸው ይታወሳል።

 

Share.

About Author

Leave A Reply