ጠ/ሚ አብይ አህመድ አፍሪካውያን የዲጂታል መታወቂያ በአስቸኳይ መጠቀም መጀመር አለባቸው ሲሉ አሳሰቡ

Google+ Pinterest LinkedIn Tumblr +

የአፍሪካ ህብረትና የተባብሩት መንግስታት ድርጅት የአፍሪካ ኢኮኖሚክ ኮሚሽን “ዲጂታል ማንነት ለ2030 የልማት አጀንዳና ለአፍሪካ ህብረት አጀንዳ 2063” በሚል ርእስ ከፍኛተኛ መድረክ በአዲስ አበባ ተካሂዷል።

በመድረኩ ላይ የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድ እና የአፍሪካ ህብረት የወቅቱ ሊቀመንበርና የሩዋንዳ ፕሬዚዳንት ፖል ካጋሜ ተገኝተዋል።

እንደ ጠቅላይ ሚኒስትር ፅህፈት ቤት መረጃ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድ የተባብሩት መንግስታት ድርጅት የአፍሪካ ኢኮኖሚክ ኮሚሽን ዲጂታል ማንነት ኢኒሺዬቲቭ አማካሪ ቦርድ ተባባሪ ሊቀመንበር ናቸው።

በዚህ መድረክ ላይ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ በተለይም የዲጂታል ምጣኔ ሀብት እያሳየ የሚገኘውን እድል ከግምት ውስጥ በማስግባት የአፍሪካን ልማት በትክክለኛ ህገ ደንቦች የሚመራ ዲጂታል አሰራር ከፍ ማድረግ አስፈላጊ መሆኑን ተናግረዋል።

አያይዘውም አፍሪካ ለተጠናከረ የንግድና የህዝቦች እንቅስቃሴ የዲጂታል እድሎችን በኢ-ገቨርናንስ ማእቀፍ ስር በአፋጣኝ መጠቀም እንዳለባትም ነው የገለፁት።

Share.

About Author

Leave A Reply