ጠ/ሚ አብይ አህመድ ከአስመራ መልስ ከተባበሩት በንግስታት ድርጂት ዋና ጸሀፊ ጋር ይወያያሉ

Google+ Pinterest LinkedIn Tumblr +

ትናንት እሁድ በኤርትራ ዋና ከተማ አስመራ በመገኘት ለሁለት አስርት አመታት የዘለቀውን ጦርነት አልባ ስጋት አስወግደው የተለያዩ ስምምነቶችን የፈጸሙት ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ከተባበሩት መንግስታት ድርጂት ዋና ጸሀፊ አንቶኒዮ ጉተረስ ጋር እንደሚወያዩ ተዘግቧል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በትናንትናው ንግግራቸው ላይ ኢትዮጵያ ከኤርትራ ጋር ያቋረጠቻቸውን ግንኙነቶች በአፋጣኝ እንደምትጀምርና የሁለቱም ሀገራት ኤምባሲዎች እንዲከፈቱ፣ የቀጥታ የስልክ መስመሮች ስራቸውን እንዲጀምሩ እንዲሁም ኢትዮጵያ በኤርትራ ወደቦች አገልግሎት ማግኘት እንደምትጀምር አሳውቀዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትር አቢይ አህመድ የስምምነቶቹን ዝርዝር ዛሬ ይፋ ያደርጋሉ ተብሎ የሚጠበቅ ሲሆን ምሽቱን ወደ አዲስ አበባ እንደተመለሱ ከተባበሩት መንግስታት ድርጂት ዋና ጸሀፊ ጋር ውይይት ለማድረግ ቀጠሮ እንደተያዘላቸው ለማወቅ ተችሏል።

ዋና ፀሃፊ አንቶኒዮ ጉተሬዝ የአፍሪካ ህብረት እና የተባበሩት መንግስታት ድርጅት 2ኛው የጋራ ጉባኤ ላይ ለመካፈል አዲስ አበባ ናቸው።- ቃሊቲ ፕሬስ

Share.

About Author

Leave A Reply