ጠ/ሚ ዶክተር አብይ አህመድና ፕሬዚዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ እየተወያዩ ነው

Google+ Pinterest LinkedIn Tumblr +

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድና ፕሬዚዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ የሁለትዮሽ ምክክር ጀምረዋል።

መሪዎቹ የሃገራቱን ህዝቦች የጋራ ፍላጎት፣ እኩልነትና ሉዓላዊነትን ከግምት ውስጥ ያስገባ ውይይት እያደረጉ መሆኑን፥ የኤርትራ ማስታወቂያ ሚኒስትር አቶ የማነ ገብረመስቀል ተናግረዋል።

ሚኒስትሩ አያይዘውም መሪዎቹ ፈጣንና አወንታዊ ውጤት የሚያስገኝ ውይይት እያደረጉ መሆኑንም ነው የተናገሩት።

የኢፌዴሪ ጠቅላይ ዶክተር አብይ አህመድ የኢትዮጵያና ኤርትራ ግንኙነትን ያድሳል የተባለለትን ታሪካዊ ጉብኝት ለማድረግ ዛሬ አስመራ መግባታቸው ይታወሳል።

አስመራ ሲገቡም ፕሬዚዳንት ኢሳያስ አፈወርቂን ጨምሮ የሃገሪቱ ከፍተኛ ባለስልጣናት እና የአስመራ ነዋሪዎች ደማቅ አቀባበል አድርገውላቸዋል።

Share.

About Author

Leave A Reply