ጠ/ሚ ዶክተር አብይ አህመድ ወደ ቻይና አቀኑ

Google+ Pinterest LinkedIn Tumblr +

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ ማምሻውን ወደ ቻይና አቀኑ። ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከፊታችን ሚያዚያ 17 እስከ 19 ቀን በቤጂንግ በሚካሄደው የቤልት ኤንድ ሮድ ኢኒሼቲቭ ፎረም ላይ ለመሳተፍ ነው ወደ ቻይና ያቀኑት።

ከአምስት አመት በፊት የተጀመረው ይህ ኢኒሼቲቭ ሃገራትን በትራንስፖርትና በመሰረተ ልማት ዝርጋታዎች ለማገናኘት ያለመ ነው። ቻይናም ኢኒሼቲቩ አብረው በትብብር የሚሰሩ የማዕቀፉ አባል ሀገራትን በተጨባጭ የሚጠቅም መሆኑን ትገልጻለች።

የመጀመሪያው የኢኒሼቲቩ ፎረም ከሶስት አመት በፊት የተካሄደ ሲሆን፥ የአሁኑ ለሁለተኛ ጊዜ የሚካሄድ ይሆናል።

Share.

About Author

Leave A Reply