ጠ/ሚ ዶ/ር አብይ በኢትዮጵያ ቅዱስ ቁራን ማህበር የአዲስ አበባ የወላጅ አጥ ችግረኛ ቤተሰቦች ልጆች ትምህርት ቤት በመገኘት የአረፋ በዓልን አከበሩ

Google+ Pinterest LinkedIn Tumblr +

አዲስ አበባ ፣ ነሃሴ 4 ፣ 2011 (ኤፍ ቢ ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ በኢትዮጵያ ቅዱስ ቁራን ማህበር የአዲስ አበባ የወላጅ አጥ ችግረኛ ቤተሰቦች ልጆች ትምህርት ቤት በመገኘት የአረፋ በዓልን አከበሩ።

ትምህርት ቤቱ ከ1 ሺህ 200 በላይ ተማሪዎችን በአሁኑ ወቅት ተቀብሎ በማስተማር ላይ ይገኛል። ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ በበዓሉ ላይ ባስተላለፉት መልዕክት መላው ኢትዮጵያዊ በዘርና በሀይማኖት ሳይከፋፈል አንዱ ሌላውን በማገዝ ችግርን ከሀገር እናጠፋለን ብለዋል።

አሁን ላይ ማህበሩ እያከናወነ ያለው ተግባር ለዚህ ጥሩ ማስተማሪያ መሆኑንም ነው ያመለከቱት። በትምህርት ቤቱ ህፃናትን የሚረዱ ዜጎች አንድ ዜጋ የሚጠበቅበትን ሀላፊነት እየተወጡ መሆኑን ነው አንስተዋል።

ሰው ማለት ከራሱ አልፎ ለሌላውም የሚኖር ማለት መሆኑንም ተናግረዋል። የማህበሩ ዋና ስራ አስኪያጅ ሀጂ መሀመድ አወል ነጃ በበኩላቸው ጠቅላይ ሚኒስትሩን አመስግነው፥ ማህበሩ ህፃናትን ለማስተማር የቦታ ጥበት ያለው በመሆኑ መንግስት ድጋፍ እንዲያደርግላቸው ጠይቀዋል።

Share.

About Author

Leave A Reply