ጥሩ ነገር ስናይ ‹‹ራስ መሳም›› እና ማመስገን ጥሩ ነው።

Google+ Pinterest LinkedIn Tumblr +

አቤል ብርሀኑ (የወይኗ ልጅ)

አንባቢዬ ሆይ ይህ ከንቱ ውዳሴ ወይም ማስታወቂያ አይደለም ከመሰለህም ስንት ኮሽኳሻ ነገር በማስታወቂያ ሲንጫጫ በሚውልበት ጊዜ ይህንን መሳይድንቅ ስራ በማስተዋወቄ እኮራለሁ

ሚዲያው በበሳል ስራዎች ድርቅ በተመታበት በዚህ ሰዓት ይህንን ድራማ ማየት እውነት ጭው ያለ ሃሩር በረሀ ላይ ዝናብ እንደማየት ደስታ ይፈጥራል በተለይየኪነ ጥበብ ጥም የዓይኑን ገሮሮ ላደረቀው ሰው፡፡ የዚህ ድራማ ጠንካራ ጎን አንድ ብቻ አይደለም እልፍ ነው፡፡

ይዞት የመጣው ታሪክ በዓይነቱ ልዩ መሆኑ ድራማውን እስከዛሬ ድራማ ካየሁበት ዓይን በተለየ መልኩ እንዳየው አድርጎኛል ፡፡ ሁሉም ገፀ ባህሪያት የተዋቀሩትጥንቅቅ ተደርገው የተሳሉና ሁሉም የራሳቸው ቀለም ያላቸው ድንቆች ናቸው፡፡

ተዋንያን መረጣም ላይ ቢሆን አስገራሚ ነው ቤተሰብ ተብለው የምናያቸው የማርታ ጌታቸው የመሳይ ተፈራ የናኦድ ለማ መመሳሰል የምር ቤተሰብ ነው ብዬእንዳምን አስገድዶኛል፡፡ ሙሉ ለሙሉ ለማለት በሚያስደፍር ሁኔታ ለቦታው የሚመጥኑ ተዋንያን ናቸው ተፈሪ ዓለሙና ከደበበ እሸቱ እስከ ዓለማየሁ ታደሰ እናአዜብ ወርቁ ከመሳይ ተፈራ እና ከአቤል ሀጎስ እስከ ማርታ ጌታቸው ከፋንታ ስንታየሁ እስከ አድማሱ ከበደ ከ እስከ ያሉት ተዋንያን ሁሉ የእውነትም ገፀባህሪውን መስለው ሳይሆን ሆነው ነው የሚሰሩት፡፡ ይህ ደግሞ የዳይሬክተሯን ብቃት ቁልጭ አድርጎ ያሳያል፡፡

ቅር ያለኝ ነገር

በነ ተፈሪ ዓለሙ ቤት ውስጥ ከባድ ጭንቀት የፈጠረች ድራማው አንድ ብሎ ከጀመረበት እለት አንስቶ ሲነገረን የነበረው የሟቿ ዓለሜ አሟሟት ነው፡የአለሜአሟሟት እንደኔ ድራማውን የሚመጥን አይደለም ባይ ነኝ፡፡ ሲሽከረከሩ በመኪና ውለው አንድ ጊቢ ውስጥ በመኪና ተገጭታ ሞተች ብዬ ለማሰብተቸግሬያለሁ፡፡ የተሻለ ነገር ቢፈለግ ጥሩ ነበር (ያው አስተያየት መስጠት እንደመስራት ከባድ አይደለም።)

በመጨረሻ ለደራሲና ዳይሬክተር መአዛ ወርቁ ያለኝን ከፍ ያለ አድናቆትና ክብር ስገልፅ በደስታ ነው፡፡ የእውነት መአዚ ራስ መሳምን የመሰለ ድርጅት አቋቁመሽእኛንም ከተለመዱ (ተዋደው ተጣሉ) (አፍቅሮ መርዝ ጠጣ) (አስረግዞ ካዳት) እና መሰል ክሊሼ ታሪኮች ነፃ ሆነን እጅግ በጣም አስፍተን እንድናስብ አድርጎናልእውነት ነው ‹‹ማንም ሰው ቢወራ ደስ የማይለው ቆሻሻ ታሪክ አለው›› ይህ የገዘፈ ሃቅ ነው፡፡

አርቲስት መአዛ ወርቁ የደርሶ መልስ ድራማ ደራሲና አዘጋጅ

Share.

About Author

1 Comment

Leave A Reply