ጥቃቱ ያነጣጠረው ንፁሀን ዜጎች ላይ ነበር

Google+ Pinterest LinkedIn Tumblr +

በመተከል ዞን አካባቢ በተፈፀመ ጥቃት ከ30 በላይ ሰዎች ተገድለዋል  18 ገደማ ደግሞ ቆስለዋል ሲል የቤንሻንጉል ክልል መስተዳደር ገለጸ።
የቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል ፕሬዝደንት አቶ አሻዲል ሀሰን እንደተናገሩት ሰኞ አነጋጉ ላይ በመተከል ዞን አካባቢ በተፈፀመ ጥቃት ከ30 በላይ ሰዎች መገደላቸውን ገልፀው 18 ገደማ ቆስለዋል ብለዋል።

ፕሬዝደንቱ አክለውም ጥቃት አድራሾቹ “ከአማራ ክልል የመጡ ታጣቂዎች” እንደሆኑ ገልፀው ወደ 85 ገደማ የሚሆኑት ከ1,500 መሳርያ እና ጥይት ጋር በመከላከያ ተይዘዋል ብለዋል።

ጥቃቱ ያነጣጠረው ንፁሀን ዜጎች ላይ እንደነበር አክለው ገልፀው ይህም ከወራት በፊት በክልሉ ላይ የተፈፀመውን ሰፋ ያለ ጥቃት እንደሚመስል አስረድተዋል።

Share.

About Author

Leave A Reply