ጥብቅ_ማሳሰቢያ!! ነገ ለፓርላማ የሚቀርበው የስደተኞች_አዋጅ መሠረታዊ ዓላማ የጋምቤላ ክልልን ከኢትዮጵያ መገንጠል ነው!!

Google+ Pinterest LinkedIn Tumblr +

ባለፈው አመት ሰኔ ላይ ለፓርላማ ቀርቦ የነበረው “የስደተኞች አዋጅ” ነገ ምክር ቤቱ ሊያፀድቀው እንደሆነ ሰምቻለሁ፡፡ አንድ ለፓርላማው ቅርበት ያለው ግለሰብ እንደነገረኝ ምክር ቤቱ በአዋጁ ላይ በአግባቡ ሳይወያይ ነው ነገ ለማፅደቅ ሽር ጉድ እየተባለ ያለው፡፡ አዋጁ በሀገሪቱ ላይ ከፍተኛ የደህንነት ስጋት የሚያስከትል ነው፡፡ በአዋጁ መሠረት ከ1ሚሊዮን በላይ ስደተኞች በሀገሪቱ ውስጥ በነፃ እንዲንቀሳቀስ የሚፈቅድ ነው፡፡

አዋጁን አሁን ማፅደቅ ያስፈለገበት መሠረታዊ ምክንያት:-
1ኛ) በተለይ #በጋምቤላ የሚገኙ የደቡብ ሱዳን ስደተኞችን ከካምፕ እንዲወጡና በጎሳና ቋንቋ ተመሣሣይ ከሆነው ከክልሉ ህዝብ ጋር ተቀላቅለው እንዲኖሩ ለማድረግ፣
2ኛ) የደቡብ ሱዳን ስደተኞች ከነባሩ የጋምቤላ ህዝብ አብላጫ ቁጥር እንዲኖራቸው ማድረግ፣
3ኛ) በመቀጠል በጋምቤላ ክልል #ኢትዮጵያ_ወይስ #ደቡብ_ሱዳን የሚል ህዝበ-ውሳኔ በማካሄድ ጋምቤላን ከኢትዮጵያ ለመገንጠል ነው፡፡ ስለዚህ የስደተኞችን አዋጅ በነገው ዕለት ማፅደቅ ኢትዮጵያ እንድትፈርስ መፍቀድ ነው፡፡

ከዚህ ቀደም በኢሜል በደረሰኝ ዝርዝር መረጃ መሠረት በብሔራዊ መረጃና ደህንነት የስደተኞች ጉዳይ አስተዳደር መምሪያ ስር በሃላፊነት የሚሰሩ የህወሓት አባላት በከፍተኛ የዘረፋና ሌብነት ተግባር የተሰማሩ ናቸው፡፡ ለፓርላማ የሚቀርበው የስደተኞች አዋጅ ባለፈው አመት የረቀቀው እና ነገ እንዲፀድቅ እየተሯሯጡ ካሉት #የጌታቸው_አሰፋ ተላላኪዎች ውስጥ የሚከተሉት ይገኙበታል፦

1ኛ) አቶ #እስጢፋኖስ ገ/መድህን ፡- የስደተኞች ህግ እና ፕሮቴክሽን መምሪያ ሃላፊ – በኩባ ዲፕሎማት ሆነዉ የተመደቡ፡፡

2ኛ) አቶ #ሃይለስላሴ ገ/ማሪያም በመምሪያዉ ምክትል ሃላፌ ከዚህ በፊት በ1997 የአዲስ አበባ ደህንነት ኃለፊ ሆነዉ የሠሩ – በእስራኤል ዲፕሎማት ሆነዉ የተመደቡ፡፡

3ኛ) አቶ #ተመስገን… ከዚህ በፊት የብሄራዊ መደረጃና ደህንነት አገልግሎት ጽ/ቤት ኃላፊ እና የአቶ ጌታቸዉ አሰፋ ረዳት የነበሩ በአሁኑ ወቅት የስደተኞች ጉዳይ አስተዳደር የምክትል ዳይሬክተሩ አማካሪ በመሆን እየሠሩ የሚገኙት- በደቡብ ሱዳን ዲፕሎማት ሆነዉ የተመደቡ፡፡

4ኛ) አቶ #ከበደ_አባይነህ – የሰዉ ሃብት መምሪያ ሃላፊ – በስዊድን ዲፕሎማት ሆነዉ የተመደቡ እና ሌሎች የህወሓት አባላትና ተላላኪዎች ናቸው፡፡

(ስዩም ተሾመ)

Share.

About Author

Leave A Reply