ጨዋታው በድጋሜ ተራዘመ።

Google+ Pinterest LinkedIn Tumblr +

የኢትዮጵያ ቡና እና የመቀሌ 70 አንድርታ እግር ኳስ ቡድኖች ጨዋታ በድጋሜ መራዘሙ ታወቀ ።

በ27ኛ ሳምንት የኢትዮጵያ ፕሪሚዬር ሊግ ሊካኤድ የነበረው የኢትዮጵያ ቡና እና የመቀሌ 70 እንድርታ ጨዋታ ግንቦት 29/2011ዓ.ም እንደሚካሄድ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌደሬሽን አስታወቀ።

በ27ኛ ሳምንት በአዲስ አበባ ስታዲዬም ግንቦት 25/2011 ዓ.ም ሊካሄድ የነበረው የኢትዮጵያ ቡና እና የመቀሌ 70 እንድርታ ጨዋታ በጸጥታ ስጋት ምክንያት መሰረዙ ይታወቃል። ጨዋታው በጸጥታ ስጋት ምክንያት አለመካሄዱን ተከትሎ የሊግ ኮሚቴው ግንቦት 27/2011ዓ.ም በአዳማ አበበ ቢቂላ ስታዲዬም ያለ ተመልካች (በዝግ) እንዲካሄድ መወሰኑን ፌዴሬሽኑ አስታውቆ ነበር።

ይህንንም ተከትሎ የኢትዮጵያ ቡና እግር ኳስ ቡድን ውሳኔውን በመቃወም ደብዳቤ አስገብቷል።

ትናንት ማምሻውን ባወጣው ማሻሻያ ደግሞ በ27/09/2011 ዓ.ም የዒድ አል ፈጥር በዓል የሚከበርበት ስለሆነ የሁለቱ ቡድኖች ጨዋታ ሐሙስ ግንቦት 29/2011ዓ.ም በአዳማ አበበ ቢቂላ ስታዲየም 9: 00 ላይ ያለ ተመልካች (በዝግ) ይካሄዳል ብሏል።

Share.

About Author

Leave A Reply