“ፓርቲያችን ጣና ሃይቅ ላይ የመጀመሪያውን ቅድመ ምስረታ ጉባኤ አደረገ እንጂ ገና አልተመሰረተም” የአማራ ብሄራዊ ሸንጎ

Google+ Pinterest LinkedIn Tumblr +

የአማራ ህዝብ በኢትዮጵያ ውስጥ ሊያገኝ የሚገባውን ጥቅም እና ሰብአዊ መብቱን ለማስጠበቅ በፓርቲ ደረጃ ለመቋቋም እየተንቀሳቀሰ ያለው “የአማራ ብሄርተኝነት ሸንጎ” የቅድመ መመስረቻ ጉባኤውን እያደረገ እንደሆነ ገልጿል።

ፓርቲው አሁን በኮሚቴ ደረጃ በመንቀሳቀስ ላይ ነው ያሉት ከአስተባባሪዎቹ መካከል አንዱ የሆኑት አቶ ተመስገን ተሰማ ናቸው።

አቶ ተመስገን ተሰማ አዲስ ጊዜ ከተባለው መጽሄት ጋር ባደረጉት ቃለ መጠይቅ “የአማራ ህዝብ ንብረቱን ተቀምቶና ተቃጥሎበት ተባሯል፣ አካለ ስንኩል ሆኗል፣ ተገድሏል፣ በዘለፋና በስድብ የህሊና ቁስል እንዲያተርፍ ተደርጎ ተዋርዷል፣ ታስሯል፣ ተሰዷል፣ በአጠቃላይ ያልደረሰበት ግፍ የለም። ከሁሉ የሚያሳዝነው አማራ በመሆኑ ብቻ መገለሉና መዋረዱ አንሶ የአሸባሪነት ካባ ተጠልቆለታል። በዚህም ተሰቃይቷል። ይህንና ይህን መሰል ስውርና ቀጥታ ጥቃቶች ለመከላከል ስንደራጅ ቢያንስ ቡድናዊ መብታችንን እናስከብራለን በሚል ነው።” ሲሉ ገልጿል።

ይህንንም ለማድረግ “የአማራ ብሄርተኝነት ሸንጎ” ፓርቲ በቅርቡ ይመሰረታል ብለዋል። ለዚህም  “በጣና ሃይቅ ላይ የመጀመሪያውን ቅድመ ምስረታ ጉባኤ አካሂደናል” ብለዋል አቶ ተመስገን ተሰማ

Share.

About Author

Leave A Reply