ፓትርያርኩ ለስድስት ቀናት ጉብኝት ሩሲያ ገብተዋል

Google+ Pinterest LinkedIn Tumblr +

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን ፓትርያርክ ብፁእ ወቅዱስ አቡነ ማቲያስ በሩሲያ ጉብኝት እያደረጉ ነው። ፓትርያርኩ በሩሲያ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ፓትርያርክ ኪሪል ግብዣ ነው ወደ ሩሲያ ያቀኑት።

የስድስት ቀናት ጉብኝት የሚያደርጉት ብፁእ ወቅዱስ አቡነ ማቲያስ ጉብኝታቸውን በዛሬው እለት በይፋ ጀምረዋል። በዛሬው እለትም ብፁእ ወቅዱስ አቡነ ማቲያስ ከሩሲያ ተጠባበቂ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሰርጌ ላቭሮቭ ጋር ተገናኝተው ተወያይተዋል።

በውይይታቸውም የሩሲያው ተጠባበቂ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሰርጌ ላቭሮቭ በኢትዮጵያ እና በሩሲያ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያናት መካከል ያለውን ታሪካዊ ግንኙነትን ሞስኮ በበጎ መልኩ እንደምትመለከተው አብራርተዋል።

ሁለቱ ቤተክርስቲያናት በዓለም ዙሪያ መቻቻል እና ሰላም እንዲሰፍን በማድረግ ላይ የበኩላቸውን ሚና መጫወት እንደሚችሉም ላቭሮቭ ተናግረዋል። ብፁእ ወቅዱስ አቡነ ማቲያስ እና ሰርጌ ላቭሮቭ ባደረጉት ቆይታም በኢትዮጵያ እና በሩሲያ መካከል ያለው የጠበቀ ታሪካዊ ግንኙነት የበለጠ ማሳገድ በሚቻልበት መንገድ ላይ መክረዋል።

Share.

About Author

Leave A Reply