ፕሬዚዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ እና ፕሬዚዳንት መሃመድ አብዱላሂ ፋርማጆ ባህር ዳር ገቡ

Google+ Pinterest LinkedIn Tumblr +

የኤርትራው ፕሬዚዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ እና የሶማሊያው ፕሬዚዳንት መሃመድ አብዱላሂ ፋርማጆ ባህር ዳር ከተማ ገብተዋል።

መሪዎቹ ዛሬ ማለዳ ላይ በጎንደር ከተማ ያደረጉትን ጉብኝት አጠናቀው ነው ባህር ዳር የገቡት።

ጠዋት ጎንደር ከተማ በነበራቸው ቆይታ በጎንደር ዩኒቨርሲቲ እና በደምቢያ ወረዳ የመስኖ ልማት ፕሮጀክቶችን ጎብኝተዋል።

ከዚህ ባለፈም ከሰዓት በኋላ የቡሬ የተቀናጀ የግብርና ኢንዱስትሪ ማቀነባበሪያ ፓርክም ጉብኝት አድርገዋል።

በባህር ዳር ከተማ በሚኖራቸው ቆይታም ከኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ ጋር የሶስትዮሽ ውይይት ያደርጋሉ ሲል የዘገበው ኤፍ ቢ ሲ ነው።

Share.

About Author

Leave A Reply