ፕሬዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ ወደ አዲስ አበባ ሊመጡ ነው

Google+ Pinterest LinkedIn Tumblr +

የኤርትራው ፕሬዚደንት ኢሳያስ አፈወርቂ (ወዲ አፎም) ቅዳሜ ረፋዱን አዲስ አበባ ይገባሉ ተብሎ ይጠበቃል።

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት የመረጃ ምንጮች እንዳረጋገጡት፤ ፕሬዝዳንት ኢሳያስ የፊታችን ቅዳሜ ሀምሌ 7 ረፋዱን አዲስ አበባ ይገባሉ ተብሎ ይጠበቃል።
የፕሬዝዳንቱን ጉብኝት የተሰካ ለማድረግም ከወዲሁ የተለያዩ ቅድመ ዝግጅቶች እየተደረጉ መሆኑንም ምንጮቻችን ገልጸዋል።

ባሳለፍነው ሳምንት የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ በኤርትር አስመራ በነበራቸው ቆይታ በማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ፖለቲካዊ ጉዳዮች ላይ ውጤታማ ውይይት ማድረጋቸውና ልዩ ልዩ ስምምነቶችን መፈጸማቸው የሚታወስ ነው።

ይህንን ስምምነት ተከትሎም በአሁኑ ወቅት ተጨባጭ ተግባራት እየተከናወኑ ይገኛሉ፤ በዋናነትም ከ20 ዓመታት በኋላ በሁለቱ አገራት መካከል የስልክ ግንኙነት ተጀምሯል፤ የኢትዮጵያ አየር መንገድም ወደ አስመራ በረራ ለማድረግ ቀን ቆርጧል።

የኤርትራው ፕሬዝዳንት የኢትዮጵያ ጉብኝትም የተጀመሩትን ለውጦች አጠናክሮ ያየስቀጥላል ተብሎ ይጠበቃል።
በፍዮሪ ተወልደ

Share.

About Author

Leave A Reply