ፖሊስ አዲስ አበባ ውስጥ ባካሄደው አሰሳ በርካታ የተደራጀ ወንጀል ተጠርጣሪዎችን ያዘ

Google+ Pinterest LinkedIn Tumblr +

ፖሊስ አዲስ አበባ ከተማ ውስጥ ቅዳሜና እሁድ ባካሄደው ዘመቻ የተለያዩ ወንጀሎችን በተደራጀ መልኩ ሲፈፅሙ ነበሩ ያላቸውን ተጠርጣሪዎች መያዙን አስታወቀ።

ፖሊስ በቁጥጥር ስር ካዋላቸው ሰዎች በተጨማሪ ለወንጀል ተግባር ሲውሉ የነበሩ ተሽከርካሪዎችን በቁጥጥር ስር መዋላቸውን ተመልክቷል። የከተማዋ ፖሊስ ኮሚሽን ምክትል ኮሚሽነር ዘላለም መንግስቴ ጉዳዩን አስመልክተው እንደተናገሩት በልደታ፣ በንፋስ ስልክ ላፍቶ እና በቦሌ ክፍለ ከተሞች በተካሄደ ዘመቻ እና ድንገተኛ ፍተሻ ሰነድ ሳይኖራቸው እና ህጋዊ ያልሆኑ 260 ተሽከርካሪዎችን በቁጥጥር ስር አውሏል።

ፖሊስ ከዚህ በተጨማሪም ህገ ወጥ የጦር መሳሪያና የመድሃኒት ዝወውርን ጨምሮ በተለያዩ የወንጀል ድርጊቶች ላይ ሲሳተፉ የነበሩ ተጠርጣሪዎችም መያዛቸው ተነግሯል።

በተጨማሪም በተለያዩ ክፍለ ከተሞች ውስጥ በተደረጉ አሰሳዎች ከ2500 በላይ የሺሻ ማጨሻዎች በድርጊቱ ከተሰማሩ ሰዎች ጋር መያዛቸውን ፖሊስ ገልጿል።
አሰሳው በተካሄደበት ወቅት ሺሻ ሲያጨሱ የተገኙ በርካታ ሰዎች እንደነበሩና በምክር እንደተለቀቁም ተገልጿል።

Share.

About Author

Leave A Reply