የ አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ መጽሃፍ በገብያ ላይ ዋለ

Google+ Pinterest LinkedIn Tumblr +

አቶ አንዳርጋቸው ትሁት በመሆኑ የመፅሃፉ ድራፍት ወደ ማተሚያ ቤት ከመሄዱ በፊት ኮመንት እንዳደርግ እንደሚፈልግ ነገረኝ መደናገሬ አልቀረም! “እኔ አንተን ኮመንት ማድረግ አይከብደኝም ብለህ ነው?” አልኩኝ። አቶ አንዳርጋቸው በተለይ በግል ሲያናግሩት ብዙ መናገር አያበዛም ፣አጠር አድርጎ “አንች ደሞ! Humility ሲበዛ arrogance እንደሚሆን አታውቂም? እልክልሻለሁ በአጭር ጊዜ አይተሽ ትልኪልኛለሽ” ሲል መለሰልኝ። ቀጠለ “በፈለግሽው መንገድ እይው፣የሚገባ ይግባ ፤የሚወጣ ይውጣ ለማለት እንዳትሳቀቂ፣ግን በአጭር ጊዜ ጨርሰሽ ላኪልኝ” አለኝ። “እሽ” ብዬ ልሄድ ተነሳሁ።

በሳምንቱ ኢሜሌን ስከፍት የመፅሃፉን ድራፍት አገኘሁት። ፕሪንት አድርጌ ገባሁበት! የሁልጊዜ አንደኛዬ ከሆነው “ነፃነትን የማያውቅ ነፃ አውጭ”መፅሃፍ በመንፈስም በአቀራረብም ለየት ያለ ሆኖ አገኘሁት። ያኛው የሃገራችን ፖለቲካ፣ባህል፣ፍልስፍና፣ታሪክ፣የትምህርት ስርዓት፣ስነ-ልቦና እና ሃይማኖት ተጣምረው የፈጠሩት ክፋት ልማት የተፈተሸበት ኮስተር ያለ መፅሃፍ ሲሆን ይህኛው ደግሞ ዘና ያለ ግን ደግሞ ከፀሃፊው ቁም-ነገረኛነት የተነሳ ቶሎ ወደ ቁምነገሩ የሚገባ ፣በፀሃፊው ግላዊ ታሪክ አድርጎ፣ በአዲስ አበባ ዘ-ፍጥረት አልፎ፣የኢህአፖን ውስጠ-ፓርቲ ስንክሳር ፣የመሪዎቹን ሰውኛ ዘይቤ ፣የመኢሶን ኢህአፓን ቁርቁስ ሌላኛ ስርመሰረት(እስከ ዛሬ ያልተነገረንን) ያስቃኘናል።

ይህን ሁሉ ሲያደርግ ፀሃፊው ኢህአፖነቱን ቀርቶ የወላጆቹ ልጅነቱን ሁሉ ረስቶ እንደ ባዕድ ታዛቢ ሆኖ ነው። እናቱን ይታዘባል፣አባቱንም አይምርም ፣ኢህአፖንም ይታዘባል! ይህን መፅሃፍ የሚያነብ ሰው የግርጌ ማስታወሻውን ካላነበበ ከመፅሃፉ የሚያገኘው ጥቅም እጅጉን ይጎዳል

Share.

About Author

Leave A Reply