182 ሺህ የአሜሪካ ዶላርን ጨምሮ የተለያዩ ሀገራት ገንዘብ በቁጥጥር ስር ዋለ

Google+ Pinterest LinkedIn Tumblr +

በቶጎ ጫሌ የፍተሻ ጣቢያ ከ182 ሺህ በላይ የአሜሪካ ዶላርን ጨምሮ የተለያዩ ሀገራት ገንዘብ በቁጥጥር ስር ዋለ።

ገንዘቡ በተሽከርካሪ ተጭኖ ከሌሊቱ 11 ሰዓት ላይ በቶጎ ጫሌ ኬላ መያዙን ከገቢዎች ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

በዚህም 182 ሺህ 247 የአሜሪካ ዶላር፣ 110 ሺህ 920 የተባበሩት ዓረብ ኢሚሬቶች ገንዘብ እና 235 ሺህ 375 የሳዑዲ ሪያል ከተጠርጣሪዎች ጋር በቁጥጥር ስር ውሏል።

ከዚህ ቀደምም በቶጎ ጫሌ ኬላ በርካታ ቁጥር ያለው የውጭ ሀገር ገንዘብ በቁጥጥር ስር መዋሉ የሚታወስ ነው።

Share.

About Author

Leave A Reply