2 ሺህ ሲም ካርዶች እና በርካታ ብር ከተለያዩ የባንክ ቡክ እና የክልሎች መታወቂያ ጋር ይዞ ሲንቀሳቀስ የነበረ ግለሰብ በቁጥጥር ስር ዋለ

Google+ Pinterest LinkedIn Tumblr +

2 ሺህ ሲም ካርዶች እና በርካታ ብር ከተለያዩ የባንክ ቡክ እና የክልሎች መታወቂያ ጋር ይዞ ሲንቀሳቀስ የነበረ ግለሰብ በቁጥጥር ስር ዋለ

በአንድ ሆቴል ውስጥ ማንነቱ ያልታወቀ ግለሰብ ትናንት ግንቦት 26/2011 ዓ.ም ማምሻውን 5፡30 ላይ 2 ሺህ ሲም ካርድ ፣ የተለያዩ በርካታ ብር የሚያሳዩ የባንክ ቡክ እና የተለያዩ ክልሎች መታወቂያ ይዞ ሲንቀሳቀስ በተደረገ ድንገተኛ ፍተሻ በቁጥጥር ስር መዋሉን የሐረሪ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን አስታወቀ።
ተጠርጣሪው ግለሰብ ለፖሊስ አባላት ብር 20,000 ጉቦ ሰጥቼ ልቀቁኝ ሲል የፖሊስ አባላቱ ከነገንዘቡ በቁጥጥር ስር አውለውታል ተብሏል።

ከክልሉ የፍትህና ደህንነት ቢሮ ያገኘነው መረጃ እንደሚያመለክተው ፖሊስ በግለሰቡ ላይ ሌሎች ተጨማሪ ምርመራ በማድረግ ለፍርድ ቤት በማቅረብ የደረሰበትን ውሳኔ ለህዝብ እንደሚያሳውቅ ገልጿል።

የክልሉ ነዋሪዎች አካባቢያቸውን በመጠበቅ እንዲሁም የሆቴል ቤት አከራዬች ጥንቃቄ በተሞላበት ሁኔታ የተከራይ ግለሰቦችን ማንነት በማጣራት ተገቢውን ፍተሻ በማድረግ እና አጠራጣሪ ነገሮች ሲገጥሙ በፍጥነት በአካባቢው ለሚገኝው የፓሊስ ጽ/ቤት መረጃ ማድረስ እንደሚጠበቅባቸው የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን መልዕክቱን አስተላልፏል።

(ኢ.ፕ.ድ)

Share.

About Author

Leave A Reply