3ሺህ 591 ሰዎች በይቅርታ እንዲለቀቁ ተወሰነ

Google+ Pinterest LinkedIn Tumblr +

ጉዳያቸው በመደበኛው ፍርድ ቤት ይታይ የነበሩ 3591 ታራሚዎች በይቅርታ እንዲወጡ የአማራ ክልል ካቢኔ ወስኗል፡፡

የአማራ ክልል ፍትህ ቢሮ ሀላፊ አቶ ፍርዴ ቸሩ ከሰዓት ዛሬ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ካቢኔው ይቅርታ እንዲደረግላቸው መወሰኑን ገልጸዋል፡፡

ኢሰብአዊ ድርጊት የፈጸሙ፣ሰውን አስገድዶ የሰወረ፣በሙስና ወንጀል የተጠረጠረ፣ሀሰተኛ ገንዝብ ዝውውር ላይ የተሳተፈ፣ህገወጥ የሰዎች ዝውውር እና አስገድዶ መድፈር በመሳሰሉ ወንጀሎች የፈጸመ ታራሚን ይቅርታው አይመለከትም ብለዋል፡፡

ከግንቦት 1 ጀምሮ ተግባራዊ ይሆናል፡፡ በዚህ ዓመት አጋማሽ ላይ ካቢኔው ለ2923 ታራሚዎች ይቅርታ እንዲደረግላቸው መወሰኑ ይታወሳል፡፡

Share.

About Author

Leave A Reply