33 ኩንታል የካናቢስ አደንዛዥ ዕፅ ተያዘ

Google+ Pinterest LinkedIn Tumblr +

አዲስ አበባ ፣ ግንቦት 5 ፣ 2011 (ኤፍ ቢ ሲ) መጠኑ 33 ኩንታል የካናቢስ አደንዛዥ ዕፅ ተያዘ። አደንዛዥ ዕፁ በኤፍ ኤስ አር ተሽከርካሪ ተጭኖ ወደ አዲስ አበባ ሊገባ ሲል ቱሉ ዲምቱ የፍተሻ ጣቢያ ላይ ነው የተያዘው።

አሽከርካሪው ከላይ የኮብል ስቶን የድንጋይ ንጣፍ በመጫን ካናቢሱን ከስር በማድረግ ለማስገባት ሲሞክር፥ በፌደራል ፖሊስና በጉሙሩክ የፍተሻ ጣቢያ ሰራተኞች ተይዟል።

አሁን ላይም አሽከርካሪው በቁጥጥር ስር ውሎ ምርመራ እየተደረገበት መሆኑን የቃሊቲ ጉሙሩክ ቅርንጫፍ ፅህፈት ቤት ስራ አስኪያጅ አቶ አለማየሁ አንቲቾ ተናግረዋል።

Share.

About Author

Leave A Reply