4 ሚሊየን የሚሆኑ የብሪታኒያ ህፃናት የተመጣጠነ ምግብ አያገኙም

Google+ Pinterest LinkedIn Tumblr +

በብሪታኒያ 4 ሚሊየን የሚሆኑ ህፃናት የተመጣጠነ ምግብ ማለትም ፦ፍራፍሬ፣አትክልት እና ሌሎች ለጤና አስፈላጊ የሆኑ ምግቦችን እንደማያገኙ አንድ የምግብ ተቋም ባወጣው ሪፓርት አስታወቀ።

ተቋሙ ያወጣው ሪፖርት እንደሚያመለክተው፥ የህፃናቱ ቤተሰቦች 42 በመቶ የሚሆነውን ገቢያቸውን መንግስት ያስቀመጠውን የምግብ መመሪያ ተግባራዊ ለማድረግ ወጪ የሚያደርጉ ሲሆን፥ ይህም ባለፀጋ ብሪታኒያውያን ወጪ ከሚያደርጉት 20 ከመቶ ገቢያቸው በአራት እጥፍ ብልጫ አለው።

ገቢያቸው ዝቅተኛ የሆኑ ቤተሰቦች ለተመጣጠነ ምግብ ወጪ የሚያደርጉት ዝቅተኛ በመሆኑ ከልክ ላለፈ ውድረት፣ የስኳር በሽታ እንደሚያጋልጥ እና የዜጎች የጤና ደረጃ ላይ ልዩነት የሚፈጥር ይሆናል ተብሏል።

መንግስት የቤተሰብ ወጪን ለመለካት የጀመረው ስራ በሚሊየን የሚቆጠሩ ዜጎች በተቀመጠው የምግብ መመሪያ መሰረት የተመጣጠነ ምግብ ማግኘት እንደማይችሉ ያሳየ ነው ሲሉ የምግብ ተቋሙ ዋና ዳይሬክተር አና ቴይሎር ተናግረዋል።

ይህ ሪፖርት ይፋ መሆኑን ተከትሎ የብሪታኒያ መንግስት ያስቀመጠው የምግብ መመሪያ ትክክል እንዳልሆነና ዝቅተኛ ገቢ ያላቸውን ዜጎች ግንዛቤ ውስጥ ያላስገባ ነው በማለት ቅሬታ አቅርበዋል።

ሪፖርቱ መንግስት የዜጎችን ገቢ በማሰደግ ፣ ህፃናትን በትምህርት ቤት በመመገብ እና እናቶችን ለመመገብ የሚያስችል ስርዓት በመዘርጋት ለችግሩ መፍትሄ መስጠት እንደሚገባው ያሳየ ተብላል።

በክረምት የእረፍት ወቅት ደግሞ 3 ሚሊየን የሚሆኑ ህፃናት ለርሃብ እንደሚጋጡ በቅርቡ ይፋ የሆነ ጥናት አመልክቷል።

ምንጭ፥ሲኤንኤን

Share.

About Author

Leave A Reply