9ኛው የኦህዴድ ድርጅታዊ ጉባኤ ተጀመረ

Google+ Pinterest LinkedIn Tumblr +

9ኛው የኦህዴድ ድርጅታዊ ጉባኤ በጅማ ከተማ ተጀመረ።

በጅማ ከተማ የተጀመረው ጉባዔ ‘‘የላቀ ሃሳብ ለተሻለ ድል’’ በሚል መሪ ቃል ለሚቀጥሉት ሶስት ቀናት የሚካሄድ ይሆናል።

በጉባኤው ታሪካዊ ውሳኔዎች ይተላለፋሉ ተብሎ የሚጠበቅ ሲሆን፥ ያለፉት ሶስት ዓመታት የውስጠ ድርጅት አፈጻጸም ይገመገማል፤ የኦዲትና ቁጥጥር ኮሚሽን ሪፖርትም ቀርቦ ውውይት የሚካሄድበት መሆኑን አስረድተዋል።

እንዲሁም የድርጅቱን ስያሜ፣ አርማ እና መዝሙር ለመቀየር የሚያስችል ረቂቅ ቀርቦም ውይይት እንደሚካሄድበት ይጠበቃል።

በ9ኛው ድርጅታዊ ጉባዔ ላይ የኦህዴድ ኢህአዴግ ሊቀመንበር ዶክተር አብይ አህመድ እና የድርጅቱ ምክትል ሊቀመንበር አቶ ለማ መገርሳ እንደተገኙ ተገልጿል፡፡

በጉባኤው ላይ በድምጽ የሚሳተፉ 1 ሺህ 66፣ በታዛቢነት የሚሳተፉ 250 ሰዎች መገኘታቸው ታውቋል።

በዛሬው ዕለት በጅማ ከተማ በጀመረው 9ኛው የኦህዴድ ድርጅታዊ ጉባኤ ከ6 ሺህ ሰዎች በላይ ይሳተፋሉ።

Share.

About Author

Leave A Reply